የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት ለማሳደግ ያለመ የቢዝነስ ማማከር (Business Coaching) ስምምነት ተፈረመ! ህዳር 23 ፣ 2018 አርባ ምንጭ የደቡብ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በ'GIZ / Invest for Jobs' የገንዘብ ድጋፍ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የቢዝነስ ማማከር እና አቅም ግንባታ አገልግሎት ለመስጠት ከ ጃሌ ኮንሰልቲንግ ፒኤልሲ ጋር የሥራ ውል ስምምነት ተፈራረመ። ይህ የድጋፍ ፕሮጀክት በሚከተሉት የፈጠራ እና እሴት መጨመሪያ (Value Addition) ዘርፎች ለተሰማሩ አምራቾች ትኩረት ይሰጣል፡- የአቮካዶ ዘይት አምራቾች ላይ፡ ከአቮካዶ ተረፈ-ምርት (Solid waste) የእንስሳት መኖ በማምረት እሴት እንዲጨምሩ ማገዝ፣ በፕላስቲክ ሪሳይክል ዘርፍ፡ የፕላስቲክ ጠርሙሶችን መልሶ በመቀየር የቤት ውስጥ የጽዳት ብሩሾችን (House cleaner brushes) ወደ ማምረት እንዲሸጋገሩ መደገፍ፣ በሙዝ ግንድ ፋይበር ውጤቶች ላይ፡ የወረቀት ቦርሳ (Paper bag) አምራቾች የምርት አይነታቸውን እንዲያሰፉ ቴክኒካዊ ድጋፍ መስጠት ናቸው። ስምምነቱ ለነዚህ አምራቾች የቴክኒክና የአመራር ክህሎት ስልጠና (Coaching and Mentoring)፣ ተስማሚ የቴክኖሎጂ ምክር እና የገበያ ትስስር ድጋፎችን መስጠትን ያካትታል።
Business Coaching Agreement Signed to Enhance Manufacturing Industry Productivity! December 2, 2025 – Arba Minch South Ethiopia Industrial Parks Development Corporation, with financial support from GIZ / Invest for Jobs, has signed a contractual agreement with Jale Consulting PLC to provide business coaching and capacity-building services to manufacturing industries. This support project focuses on manufacturers engaged in the following innovation and value-addition sectors: Avocado Oil Producers: Supporting them to add value by producing animal feed from avocado solid waste. Plastic Recycling Sector: Assisting enterprises to transition into producing house cleaner brushes from recycled plastic bottles. Banana Fiber Products: Providing technical support to paper bag manufacturers to help them expand and diversify their product portfolios. The agreement includes delivering technical and managerial coaching and mentoring, recommending appropriate technology, and facilitating market linkage support for these enterprises.
Jale Consulting PLC will collaborate closely with stakeholders to ensure sustainable outcomes, emphasizing continuous improvement and knowledge transfer.
